Tuesday, April 9, 2013

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም


ኢትዮጵያዊነት 
ኢትዮጵያዊነት ለሙሴ፣ ለክርስቶስና ለመሐመድ የሚጨሰው ዕጣን በእርገት መጥቶ የሚደባለቅበት እምነት ነው።
ኢትዮጵያዊነት በቄጤማ ጉዝጓዝ ላይ የሚታየው መተሳሰብና መፈቃቀር ነው።
ኢትዮጵያዊነት የአስተዋይነት፣የሚዛናዊነት የጨዋነት ባሕርይ ነው።
ኢትዮጵያዊነት ረዢምና ተጽፎ ያላለቀ ታሪክ ነው፤ ብዙ ሰዎችም የተሰዉለት ስሜት ነው።
ኢትዮጵያዊነት ስቃይና መከራ ነው፤ ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ክብርም ነው።
ኢትዮጵያዊነት ጭቆናና ጥቃት ነው፤ ኢትዮጵያዊነት አሻፈረኝና እምቢ ባይነትም ነው።
                                                   ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

“መሰላል ለመውጣት”

መሰላል ለመውጣት፤
አለው ትልቅ ብልሃት፡፡
የላዩን ጨብጦ፤
የታቹን ረግጦ፤
ወደላይ መመልከት
ብልሆች የማይጣደፉ፤
ሞልተዋል በያፋፉ!
ዘርግተው የጨበጡትን መርገጥ፤
የመውጣት ህግ ነው የማይለወጥ!
ሲወርዱ ግን ያስፈራል፤
የረገጡትን ያስጨብጣል፡፡
ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

No comments:

Post a Comment