በቅርቡ የወጣውን የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ አጭር የሕይወቱና
የጽሑፉ ታሪክ፣ ዮሐንስ አድማሱ (1929 – 1967) ጽፎ ዶ/ር ዮናስ አድማሱ አሰናስሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ያሳተመውን
መፅሀፍ ብታነቡት እንዴት ያለ ሸጋ መፅሀፍ መሰላችሁ፡፡ በነገራችን ላይ ይህ መፅሀፍ በዮሐንስ አድማሱ ተጀምሮ በታናሽ ወንድሙ በዶ/ር
ዮናስ አድማሱ የተጠናቀቀ ድንቅ ስራ ነው፡፡ ለማንኛውም በመፅሀፉ ጀርባ የሰፈረውን ጽሁፍ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርቤላችሁ መፅሀፉን
ገዝታችሁ እንድታነቡ ደግሞ እለምናችኋለሁ፡፡
/ዮፍታሔ ንጉሤ፣ ብሔረ ነገዱ፣
ሀገረ ሙላዱ፣ ጎጃም፤ ቅኔ የተቀኘበት፣ ድጓ የተማረበት፣ ምስጢር ያገመረበት ደብረ ኤልያስ ነበረ፡፡ ጠይም ረዥም፤ ጠጉረ ሉጫ፤
መልከ መልካም፤ የቆንጆ ጠር፤ ቀጭን ዠርጋዳ ጣተ መልካም፤ ሽቅርቅር ጥዩፍ፤ ኮከቡ ሚዛን ነፋስ ነበረ፡፡/ (ምዕራፍ 1)
/ዮፍታሔ/ የቀለም ትምህርቱን
ከመጀመሩ አስቀድሞ ምግበ አእምሮው የሆነውን የኤልያስን አየር እየተመገበ፣ ዝንጀሮ ያለችውን ሁሉ ዘፈኑን፣ ስለምኑን፣ ቁም ነገሩን፣
ወዘበሬታውን፣ ተረቱን፣ ድርሳነ ባልቴቱን፣ ቀረርቶውን፣ ልቅሶውን፣ እማ በራዩን፣ ሙሻሙሾውን፣ አይኮሉን፣ አረቦኑን፣ ወዘተ… እየሰማ
ነበረ ያደገው፡፡ ይኸ ሁሉ ኋላ ለተቀኘው ቅኔና ለደረሰው መዝሙር፣ ቲያትርና ስለምን ዐይነተኛ ዳራ ሆኖታል፡፡ (ምዕራፍ 1)
የቅኔ ትምህርት ተራውና
ደረጃው ከፀዋትወ ዜማ ቀጥሎ ከትርጓሜ መጻሕፍት አስቀድሞ በ ጉልምስና ወራት ነው፡፡ … ቅኔ የንባብና ከፀዋትወ ዜማ ደጀን የትርጓሜ
መጻሕፍት ፊታውራሪ ነው፡፡ … ቅኔ ከፀዋትወ ዜማ በፊት ከትርጓሜ መጻሕፍት በኋላ ለመማር በፍጹም አይቻልም፡፡ ይኸውም ከዘር በፊት
ቡቃያ ከባል በፊት ልጅ ይሆናል፡፡
...
…
…
… በዚህ ጥናት አማካይነት ዮፍታሔ ንጉሤን ለአንባቢው ለማቅረብ የሞከርሁት፣
የተቻለኝን ያህል፣ እንደ ሰው ነው- አለ አግባቡ እንዳይወደስ፣ አለ መልኩ እንዳይወቀስ፣ እንደ ግዕዙ እንዲታይ ነው፡፡ (ዮሐንስ)
…
…
…
ሁሉንም ያልጻፍኩላችሁ አይጠቅምም ብዬ ሳይሆን ገዝታችሁ እንዳታነቡት የማንበብ አምሮታችሁ
እንዲነሳሳ ብዬ ነው ከተሳካልኝ፡፡ መጨረሻ ላይ ይሄ ሰፍሯል፡-
ድንግል ሀገሬ ሆይ ጥንተ ተደንግሎ
ሕፃናቱም ታርደው ያንቺም ልብ ቆስሎ
ልጅሽ ተሰደደ አንቺን ተከትሎ
የሕፃናቱም ደም አዘክሪ ኩሎ፡፡
አስጨነቀኝ ስደትሺ
እመቤቴ ተመለሺ ተመለሺ፡፡
(“ድንግል
ሀገሬ ሆይ”)
ትምህርት እንዲስፋፋ ጉልበት እንዲጠና
አራቱ ጉባኤ ይነሡልንና
መኮንን ደረሶ አሉላ ጎበና
አገራችን ትማር አሁን እንደገና፡፡
ጎበና
ከፈረስህ
ጋራ ተነስ እንደገና፡፡
(“አጥንቱን
ልልቀመው”)
ዋጋ አንድ መቶ አስራ
አራት ብር ብቻ
No comments:
Post a Comment