በተሸበሸቡ
የአረጋዊ ጉንጮች
ላይ አንዲት የምታብለጨልጭ
የእንባ ዛላ ካ’ንድ
ጎልማሳ ዓይኖች
ከሚፈስሱ የእንባ
ዘለላዎች ሁሉ ይልቅ
ነፍስን በይበልጥ ትጎዳለች::
በጎልማሳነት ዘመን በገፍ
የሚነባው እንባ የሚጎርፈው
ከሞላች ልብ ጥጋጥግ
ሲሆን፣ ካ’ዛውንት
ሰው የሚመነጨው እንባ
ግን ካ’ይንብሌን
የሚፈስ የሒወት
እንጥፍጣፊ ነው - የተዳከመ
ሰውነት ፍድፋጅ:: በጎልማሳ
ዓይኖች ያሉ እንባዎች
በጽጌረዳ ቅጠሎች ላይ እንዳሉ
የጤዛ ጠብታዎች
ዓይነት ነው፤ ነገር ግን
ዘመን በገፋ ሰው
ፊት ላይ ያሉ እንባዎች
የሒወት ክረምት
ሲብት የሚነፍሰው
ነፋስ እንደሚጥላቸው የወየቡ
የመፀው ቅጠሎች
ዓይነት ናቸው::
ካህሊል ጂብራን ‹‹የተሰበሩ ክንፎች›› (1999)
No comments:
Post a Comment