ሰላም እንዴት ናችሁ?
የተከበራችሁ የዚህ ጦማር ታዳሚዎች፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ በተከፈተ ባጭር ጊዜ ውስጥ የምሰራበት መስሪያ ቤት የICT ባለሙያዎች
በመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በተደጋጋሚ የሚጎበኙ፣ የስራ ጊዜን የሚሻሙ፣ ጸረ-መንግስት የሆኑ፣ ለስራ አላስፈላጊና የወሲብ ድረ ገጾች
ተብለው ከተመደቡት እንደነ Facebook, Twitter, Addisnegeronline, Aigaforum, etc… ተርታ የኔም ብሎግ
ተመድቦ ታግዶ/Blocked ይገኛል (ባለኝ ስታትስቲክስ መሰረት ብዙዎቹ የጦማሩ አንባቢዎች ከምሰራበት አካባቢ ናቸው)፡፡ የመጥፋቴም
ምክንያት ይህና ሌሎች ከስራ ጋር የተገናኙ ምክንያቶች ያስከተሉት ስለሆነ ከልብ ይቅርታ እየጠየቅሁ ለአጋጆቼም ምቀኛ አታሳጣኝ እላለሁ፡፡
“Tower in
the Sky” የሚል አዲስ አበባን ያነጋገረና እያነጋገረ ያለ መጽሐፍ ብዙ ሰምታችሁ ወይም ምንም አልሰማችሁ ይሆናል ነገር ግን
አንድ ነገር በርግጠኝነት መናገር የምችለው መጽሐፉ እጅግ በጣም የሚገርም የአጻጻፍ ስልትን የተከተለ፣ ከፊልም በላይ ግልጥ አርጎ
የሚያሳይ፣ በሙሉ ቅንነትና ሀቀኝነት የተጻፈ፣ ለማመን በሚያስቸግሩ ክስተቶችና ታሪኮች የተሞላ፣ በ1960 እና 70ዎቹና የነበረውን
ትውልድ (በተለምዶ “ያ ትውልድ” የሚባለውን) አስተሳሰብ፣ አመለካከት፣ አካሄዶች፣ ስህተቶች፣ ጥንካሬዎችና ድክመቶች ነቅሶና አጥርቶ
ያወጣ፣ እንዲሁም እውነት እንደሆነ በሁሉም ባለድርሻዎች የተመሰከረለት እጅግ እጅግ በጣም ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡
መጽሐፉ በሕይወት ተፈራ
በእንግሊዘኛ ቋንቋ ተጽፎ በአዲሰ አበባ የኒቨርሲቲ ፕሬስ የታተመ ሲሆን በ437 ገጾች ለየት ያለ ግለ-ታሪክና ስለ ዘመኑና የጸሓፊዋን
ምልከታ (Impression) ይተርካል፡፡ መጽሐፉ የባለ ታሪኳን የሕይወት ጉዞ ከዘናጭና ፈታ ያለች ፍሬሽ የዩኒቨርሲቲ ተማሪነት
እስከ መካከለኛ የኢሕአፓ (የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ) አመራር/ አባልነት ያለውን አስፈሪ፣ አደገኛ፣ ሚስጥራዊ፣ በጀግነትና
በእድል የተሞላ ታሪክ ያስነብባል፡፡
ሕይወት በመጽሐፏ አራት
አስርት አመታትን ወደ ኋላ ወስዳ የነበራትን የፓለቲካ ንቃተ ህሊና፣ ለፓርቲዋ (ኢሕአፓ) እና ለአይዲዎሎጂው (ሌኒኒስት/ማርክሲስት)
የነበራትን ታማኝነትና ፅናት ይዳስሳል፡፡
ሕይወት እንደማንኛውም
ሐረር የተወልደ ልጅ ዘና ያለች መሳቅ መጫወት የምትወድ ባጭሩ ጣጣና ጭንቅ የሌለባት ወጣት ነበረች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብታ
ጌታቸው ማሩ የሚባል ወጣት ተዋውቃ ህይወቷን ባላሰበችው አቅጣጫ እስኪቀይረው ድረስ፡፡ ጌታቸው ማሩ በወቅቱ የአምስት ኪሎ የምህንድስና
በውጤቱ ስመጥር ተማሪ፣ የተማሪዎች ፕሬዝደንት የነበረ፣ እጅግ በጣም አንባቢ፣ የአብዮት ኋላ ኢሕአፓ የሆነው ፓርቲ መስራች አባል
ነው፡፡
ባጠቃላይ
“Tower in the Sky” ያለፈውን ትውልድ ትክክለኛ ታሪክ ያስቀመጠ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ አሁን ድረስ መሰረታዊ የሀገሪቷ
ችግር የሆነውን ያለመደማመጥ ችግርና ጉዳቶቹን ቁልጭ አርጋ አመላክታለች፡፡ በመጨሻም ሕይወት በቁስ ለመተመን ፈጽሞ የማይቻልና ለትውልድ
ቅርስ የሆነውን ይህንን ስጦታ በቅንነትና በነጻነት ሰርተሽ ስላበረከትሽ እጅግ የከበረ ምስጋና ይገባሻል፤ የጌታቸው ማሩን ታሪክ
ብቻ ሳይሆን የትውልዱንና የሀገሪቷን ታሪክ ነው የጻፍሽው፡፡
ፍሬዘር ማሩ
very nice. I agree.
ReplyDeleteHiwot's book was a wake up call to a lot of Ethiopians. A story of Getachew Maru and his friends who died fighting for their country.
ReplyDeleteA new book is out that tells the story and history of the generation who joined EPRP and lost their lives by the hands of their own leaders.
A must read.
Motherland! (Amharic Edition) (Amharic) Paperback – February 2, 2015
by Ayalew Mergiyaw (Author)
Enat Agere
The book is in memory of all revolutionaries and patriotic forces and individuals of the motherland who lost their lives fighting against external enemies and their home- grown collaborators (the communist military junta/derg, Shabia/EPLF, woyane/TPLF, MeIson and Ihapa/EPRP leaders in the 70s, 80s, to late 90s) while safeguarding the sovereignty and territorial integrity of their motherland and protecting its people. The sales of the book is dedicated to these gallant precious and dearest sons and daughters of the motherland. It is about freedom, democracy, unity, equality, justice and peace in the sub-region.
http://www.amazon.com/Motherland-Amharic-Ayalew-Mergiyaw/dp/0646936301/ref=sr_1_1?s=books&ie=UTF8&qid=1432682528&sr=1-1&keywords=ayalew+mergiyaw